ሀምሌ 01/2014 የወጣውን የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ Latest News in Ethiopia

Posted On: Jan 01, 1970

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሀምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል፡-

በከተማችን አዲስ አበባ ከሚስተዋሉ ችግሮች መካከል አንዱ የቤት አቅርቦት እጥረት ሲሆን ይህንኑ ደረጃ በደረጃ ለማቃለል አስተዳደሩ የተለያዩ አማራጮችን ነድፎ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የዚህ ሂደት አካል የሆነው የነባሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉበትን ወስብስብ ችግር ለይቶ በመፍታት ተመዝጋቢዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ እና የቤት እጥረት ጫና ለመቀነስ የተደረገው ሰፊ ጥረት ተጠቃሽ ነው፡፡

በዚህ ሂደት በግንባታ ላይ የነበሩ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል 25,491 ያህሉ በቅርቡ ለባለ እድለኞች የዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት መካሄዱ ይታወቃል፡፡

ይህ የቤት ማሰስተላለፍ ስራ እንደ ከዚህ በፊቱ በቆጣቢዎች መካከል አድሎና ብልሹ አሰራር እንዳይኖር ለማድረግ ግልፅነት በሚያሰፍን አግባብ ለማስተላለፍ ሲባል በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራ በመስራት ሂደቱን ግልጽና አሳታፊ ለማድረግ የተደረገው ተነሳሽነትና ጥረት እንዲሁም የባለሙያዎችን ሙያዊ ነፃነት አክብረን አስፈላጊውን ሂደት ተከትለን ተዓማኒነቱን እንዲያረጋግጡልን አድርገን ነበር:: በዚህ ሂደት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ አዲስ ሶፍትዌር እንዲበለፅግ እና ስለሶፍትዌሩ ታአማኒነት የኢኖቬንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር እንዲያረጋግጥልንም ተደርጓል::

በቀጣይም ከሁለት ጊዜ በላይ ታዛቢዎች እና ባለሙያዎች ፊት ቀርቦ እንዲያረጋግጡልን ተደርጎ ማረጋገጫ ሰጥተዋል::

ይህ ሁሉ ሂደት ከእለት ጉርሱ የቆጠበዉን እና በከፍተኛ ጉጉት የሚጠባበቀውን ሕዝብ በፍትሃዊነት ተደራሽ ለማድረግ ቀና ሃሳብ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል::

ይሁን እንጂ ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ስንጀምር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች ተግኝተዋል::

በመሆኑም በእስካሁኑ የማጠራት ስራ ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል፡፡

ከዚህ በመነሳትም የቤት ማስተላለፉን ሂደት ግልፅነት ለማስፈን ሲባል እና ውጤቱን የሚያዛባ ተግባር ሲያጋጥም መልሰን ኦዲት እንዲደረግ በገባነው ቃል መሰረት የተፈጠረውን ችግር ከጉዳዩ ገለልተኛ በሆኑ በሚመለከታቸው ተቋማት የማጣራት ስራ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በጉዳዩ የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር በቁጥጥር ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገ ይገኛል::

ስለሆነም ሂደቱን በአጭር ጊዜ አጠናቀን ለቤት ተመዝጋቢዎችና ለመላው የከተማችን ነዋሪ የምናሳውቅ መሆኑን ስንገለጽ ተመዝጋቢዎች እንደተለመደው በከፍተኛ ትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን፡፡

ለተፈጠረው ስህተት የከተማ አስተዳደሩ በዚህ አጋጣሚ ይቅርታ ይጠይቃል

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ሐምሌ 4/2014 ዓ/ም

Ads

Tags

20/80 ኮንዶሚኒየም 20/80 ኮንዶሚኒየም ቤቶች አሸናፊዎች ስም ዝርዝር 20/80 ኮንዶሚኒየም ዕጣ 2014 40/60 ኮንዶሚኒየም 40/60 ኮንዶሚኒየም 2014 ስም ዝርዝር 40/60 ኮንዶሚኒየም ቤቶች አሸናፊዎች ስም ዝርዝር 40/60 ኮንዶሚኒየም ዕጣ 2014 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ 2022 የአዲስ አበባ ቤቶች እጣ 2014 ስም ዝርዝር የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ 2014 ዝርዝር

Saachi Double Hot Plate NL-HP-2141C – Cook Twice as Fast with 2000W Power
4,500.00 ETB
Epson Perfection V19 Home Photo & Document Scanne
26,500.00 ETB
WASS Electronics 16' Digital Mitad Grill
23,000.00 ETB
midea air conditioners 18000btu split system
115,000.00 ETB
Ac air conditioners 18000-btu delivery
125,000.00 ETB
hp elitebook 840 G5Core i7-8th genaration512GB ssd STORAGE16GB RAM 
55,000.00 ETB
Epson Perfection V19 Color Photo & Document Scanner
26,500.00 ETB
MacBook pro M1 ️M1 chip 14 inch XDR display256 storage 16 GB GB
105,000.00 ETB
Video Capture Card HDMI to USB Game & Video Capture (USB 2.0 Video Capture)
2,200.00 ETB
Brand New EPSON ProjectorWith manual  CD and cartoon Model name:  EB -X49Hardware interfa
99,990.00 ETB
TOYOTA HILUX KING CAB 2008
3,400,000.00 ETB
Samsung A14 5g
15,500.00 ETB
Acer Predator Helion NEO16    Core i9 14th generation With 24-core and 32-logical process
290,000.00 ETB
New Apple Macbook pro 2019
145,000.00 ETB
TOYOTA VELOZ 2023
5,000,000.00 ETB
2-in-1 Dehydrated Self-Wringing Mop
2,900.00 ETB
Samsung Galaxy S23 Ultra 5G 256GB Dual
86,000.00 ETB
PEUGEOT 2008 2022
3,750,000.00 ETB

Ads